ሙስናን ለመከላከል የፖለቲካ አመራሩ ቁርጠኝነት ወሳኝ ነው ተባለ


ታኅሣሥ 21/2014 (ዋልታ)
ሙስናን በዘላቂነት ለመከላከል የፖለቲካ አመራሮች ቁርጠኝነት ወሳኝ መሆኑ ተገለፀ፡፡
የዓለም የፀረ-ሙስና ቀን በሐረሪ ክልል “በስነ-ምግባር የታነፀ አመራር ከሙስና ለፀዳች ኢትዮጵያ” በሚል መሪ ቃል በዛሬው ዕለት ተከብሯል፡፡
የክልሉ ስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽነር ኻሊድ ኑሬ ሙስናን ለመከላከል የፖለቲካ አመራሩ ቁርጠኝነት ወሳኝ መሆኑን ገልፀው ኅብረተሰቡም ሙሰኞችን በማጋለጥ የድርሻውን እንዲወጣ ጠይቀዋል፡፡
በተለይ የፖለቲካ አመራሮች በየተቋማቱ ያለውን የሀብት ብክነት ለማስቀረት ጠንካራ እርምጃ መውሰድ አለባቸው ብለዋል፡፡
የክልሉ ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ አሪፍ መሀመድ በበኩላቸው በስነ-ምግባር የታነፀ ትውልድ መፍጠር ከቻልን ሙስናን በዘለቄታነት መከላከል እንችላለን ብለዋል፡፡
በተለይም የሃይማኖት ተቋማት፣ የፖለቲካ አመራሮች፣ የትምህርት ተቋማትና የፍትህ አካላት ድርሻ የጎላ መሆኑን አንስተዋል፡፡
በሐረሪ ክልል የፀረ-ሙስና ቀን ሲከበር በጥያቄና መልስ አሸናፊ የሆኑ ተማሪዎችን ጨምሮ በጥሩ ስነ-ምግባራቸው ለተመረጡ አመራሮች ሽልማት ተበርክቷል፡፡
በፍስሃ ጌትነት
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት፦
የአማርኛ ፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ ይከተሉ
ከአረብኛ ፌስቡክ ገፃችን ጋርም ይጓዙ
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
የትዊተር ገፃችንን ይከተሉ
አብራችሁን ስለሆናችሁ ደስተኞች ነን!