ሚኒስቴሩ 510 ሞተር ሳይክሎችን ለክልሎች አበረከተ

ግንቦት 26/2014 (ዋልታ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ያደረገባቸውን 510 ሞተር ሳይክሎችን ለክልሎች አበርክቷል፡፡

በርክክብ ስርዓቱ ላይ የተገኙት  የውሃና ሳኒቴሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር አስፋው ዲንጋሞ፤ ተሸከርካሪዎቹ የክልሎቹን የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ የሚደግፉ መሆናቸውን ገልታ መሰል የድጋፍ ተግባር ቀጣይነት ይኖራቸዋል ማለታቸውን የኢፕድ ዘገባ አመላክቷል፡፡

ለሞተር ሳይክሎቹ ግዥ ከ105 ሚልዮን ብር በላይ ወጪ መደረጉን የገለጹት ሚኒስትር ድኤታው፤ ገንዘቡ የአለም ባንክና ሌሎችም አለም አቀፍ ግብረሰናይ ድርጅቶች ባደረጉት ድጋፍ መሸፈኑን አስታውቀዋል፡፡