ሚኒስቴሩ ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ጋር የሰው ሀይል አቅም ለማሳደግ የሚያስችል ስምምነት ተፈራረመ

የካቲት 9/2014 (ዋልታ) የግብርና ሚኒስቴር ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ጋር በመሬት አስተዳደር ዙሪያ የሰው ሀይል አቅም ለማሳደግ የሚያስችል የውል ስምምነት ተፈራርሟል።

የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ እያሱ ኤልያስ (ፕ/ር) እንደገለጹት የመሬት አስተዳደርን ለማዘመን ባለሙያዎችን በማልማት ረገድ ዩኒቨርስቲዎች የሚያደርጉትን ጥረት የቀበሌና የወረዳ ባለሙያዎችን እንዲበቁ ያስችላል።

አርሶአደሩ የ1ኛ እና 2ኛ ደረጃ የመሬት ባለቤትነት ማረጋገጫ ማግኘት እንዲችል ከፍተኛ ስራዎች መሰራታቸውንም ሚኒስትር ዴኤታው መግለጻቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

በዘርፉ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ላበረከቱት አስትዋጽኦ እውቅና የተሰጠ ሲሆን የCALM-LA ፕሮጀክት በክረምት መርሃ ግብር የሰው ሀይልን ለማብቃት የሚያስችል የውል ስምምነት ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እና ከግብርና ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ጋር ተፈራረሟል፡፡