ሚኒስቴሩ ክትትል ከሚያደርግባቸው የወጪ ንግድ ምርቶች ከ79.3 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ ገቢ ተገኘ

ታኅሣሥ 26/2014 (ዋልታ) በ2014 በጀት ዓመት የኅዳር ወር የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ክትትልና ድጋፍ ከሚደረግባቸው የወጪ ንግድ ምርቶች በገቢ 93 ሺሕ 42 ነጥብ 82 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ለማግኘት ታቅዶ 79 ሺሕ 319 ነጥብ 53 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ማግኘት እንደተቻለ ተገለጸ፡፡

በዚህም የዕቅዱን 85 ነጥብ 25 በመቶ ማሳካት እንደተቻለ ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡

አፈፃፀሙ ከአምናው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወር ጋር ሲነጻጸር በገቢ 12 ነጥብ 73 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል ነው የተባለው፡፡

ሚኒስቴሩ ክትትል የሚያደርግባቸው የወጪ ንግድ ምርቶች የቅባት እህሎች፣ የጥራጥሬ ሰብሎች፣ የተፈጥሮ ሙጫና ዕጣን፣ ጫት፣  ባሕር ዛፍ፣ የብዕርና አገዳ እህሎች እና የቁም እንስሳት መሆናቸውም ተጠቁሟል፡፡

በኅዳር ወር ከተገኘው አጠቃላይ የወጪ ንግድ 333 ሺሕ 932 ነጥብ 93 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ ውስጥ ሚኒስቴሩ ክትትል ከሚያደርግባቸው የወጪ ንግድ ምርቶች ገቢ 23 ነጥብ 75 በመቶ እንደሚሸፍን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል፡፡