ሚኒስቴሩ የተጣለበትን ኃላፊነት በብቃት እየተወጣ ነው

ሚያዝያ 27/2014 (ዋልታ) የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል ሚኒስቴሩ የተጣለበትን አገራዊ ኃላፊነት በብቃት እየተወጣ መሆኑን ገልጹ።

የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የዘጠኝ ወራት የእቅድ አፈፃፀሙን እየገመገመ ነው።

በዘርፉ የተለያዩ ማነቆዎችና የአግዋ እገዳ ቢኖርም በኤክስፖርት ረገድ ከ90 በመቶ በላይ አፈፃፀም እንደተመዘገበ ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

ይህም ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ የእቅድ አፈፃፀም ጋር ሲነፃፀር የተሻለ እንደሆነ ተመላክቷል።

አዳዲስ የኢንቨስትመንት እድሎች በማምጣት ረገድም ከእቅድ በላይ አፈፃፀም ተመዝግቧል ተብሏል።

በደምሰው በነበሩ