ሚኒስቴሩ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አባል የሆኑት ሙሉቀን ሀፍቱ (ዶ/ር) የህግ ከለላ እንዲነሳ ጥያቄ አቀረበ

ሙሉቀን ሀፍቱ (ዶ/ር)

ሐምሌ 8/2014 (ዋልታ) የፍትህ ሚኒስቴር የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አባልና የአዲስ አበባ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ኃላፊ የሆኑት ሙሉቀን ሀፍቱ (ዶ/ር) የህግ ከለላ እንዲነሳ ጥያቄ አቅርቧል፡፡

የህግ ከለላው ይነሳልን ጥያቄው ከቤቶች እጣ አወጣጥ ጋር በተያያዘ እና የተሰጣቸውን ስልጣንና ኃላፊነት በአግባቡ ባለመጠቀም በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ውለው እንዲጣራ ለማድረግ መሆኑን የከንቲባ ጽሕፈት ቤት ፌስቡክ ገጽ መረጃ ያመለክታል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት አፈጉባኤ ቡዜና አልቃድር ከፍትህ ሚኒስቴር የተላከውን ደብዳቤ ለምክር ቤቱ ባቀረቡበት ወቅት ያለመከሰስ መብታቸው እንዲነሳ መጠየቁን ተናግረዋል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW