ሚኒስቴሩ የአድዋ ድል በዓል ልክ እንደ ከዚህ ቀደሙ በሚኒሊክ አደባባይ እንደሚከበር ገለጸ

የካቲት 22/2014 (ዋልታ) 126ኛው የአድዋ ድል በዓል ልክ እንደ ከዚህ ቀደሙ በሚኒሊክ አደባባይ እንደሚከበር የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ ወርቅነሽ ብሩ አስታወቁ።

በዓሉ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና ከኦሮሚያ ክልል ጋር በመተባበር ይከበራል ተብሏል።

ማኅበረሰቡ ይህን አውቆ በማኅበራዊ ሚዲያ የሚናፈሰውን ወሬ ከእውነት የራቀ መሆኑን ሊረዳ ይገባል ነው የተባለው፡፡

ከዚህ ቀደም በእግር ጉዞ እና በተለያዩ መርሃ ግብሮች ሲከበር መቆየቱም ይታወሳል።