ሚኒስቴሮቹ የበጎ ፈቃደኝነት ቀን በጋራ እያከበሩ ነው

ጳጉሜ 1/2014 (ዋልታ) የጤና፣ የትምህርት እንዲሁም የስራና ክህሎት ሚኒስቴሮች የበጎ ፈቃደኝነት ቀንን በጋራ እያከበሩ ነው፡፡

ሚኒስቴሮቹ በጋራ የሚያዘጋጁት የሙሉ ቀን መርሐ ግብር በሚኒሊክ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ እና የመጀመርያ ደረጃ ትምህርት ቤት በተለያዩ ዝግጅቶች ተጀምሯል።

የትምህርት ተቋማትን ፅዱና ውብ በማድረግ እንደዚሁም የተተከሉ ችግኞችን በማረም፣ በመኮትኮት እና በመንከባከብ ነው መርሐ ግብሩ እየተካሄደ ያለው።

በመርሃ ግብሩ ላይ የጤና ሚኒስትር ሊያ ታደሰ (ዶ/ር)፣ የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)  እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸዉ እንግዶች ተገኝተዋል።

መርሐ ግብሩ ለ2015 የትምህርት ዘመን የትምህርት ተቋማት ለተማሪዎች ምቹ ፣ ፅዱ፣ ውብና ማራኪ እንዲሁም ሳቢ እንዲሆኑ እና ለመማር ማስተማሩ ሂደት ጉልህ ሚና እንዲኖራቸው ለማድረግ የሚያስችል እንደሆነ መገለፁን የትምህርት ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።