ቀጀላ መርዳሳ  እድሳትና ግንባታቸው ይፋጠናል የተባሉት ስታዲየሞች ጎበኙ

ጥቅምት 17/2014 (ዋልታ) የአዲስ አበባ ስታዲየም እድሳት በተያዘለት የጊዜ ገደብ ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት እንዲሆን እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ፡፡

በባህልና ስፖርት ሚኒስትሩ ቀጀላ መርዳሳ የተመራ ልዑክ የስታዲየሙ እድሳት የሚገኝበትን ሁኔታ ተመልክቷል፡፡
ስታዲየሙ ከግማሽ ምዓተ አመት በላይ ያስቆጠረ እንደመሆኑ ዘመኑን የሚመጥን ሆኖ እንዲታደስ እየተሰራ ነው ተብሏል፡፡
ከአዲስ አበባ ስታዲየም በተጨማሪ በግንባታ ላይ የሚገኘው የአደይ አበባ ብሔራዊ ስታዲየምም ተጎብኝቷል፡፡
ሚኒስትሩ ግንባታው የገጠመውን የውጭ ምንዛሬ ችግር በአስቸኳይ በመፍታት ኢትዮጵያ የዘመናዊ ስታዲያም ባለቤት እንድትሆን ይሰራል ብለዋል፡፡
በትዝታ ወንድሙ