ማህበረሰቡ የህወሃትን የሃሰት መረጃ ባለማሰራጨት እኩይ አላማውን ሊያከሽፍ እንደሚገባ ተገለጸ

ነሀሴ 12/2013 (ዋልታ) – ማህበረሰቡ የአሸባሪውን የህወሃት ቡድን የሃሰት መረጃ ባለማሰራጨት የጥፋት ቡድኑን እኩይ አላማ ሊያከሽፍ እንደሚገባ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አህመድ እድሪስ አሳሰቡ፡፡

ዳይሬክተሩ አሸባሪውን የህወሃት ቡድን ለመመከት የህዝቡ አንድነት የሚበረታታ መሆኑን በመግለፅ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የኢጋድ ጉዳዮች ዋና ዳይሬክተር ፍስሀ ሻወል የጥፋት ቡድኑ በስልጣን ላይ በነበረበት ወቅት የኢትዮጵያን ታላቅ ስም ለመጠሪያ ብቻ በመጠቀም ብሄርን ከብሄር በመለያየት የሰራ ሲሆን አሁንም ይህንን እኩይ አላማቸውን ለማሳካት ቆርጠዉ መነሳታቸውን ህዝቡ ሊገነዘብ ይገባል ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያን እድገት እና ሰላም ለማደናቀፍ የተነሱትን የውጭና የውስጥ  ጠላቶች ለመመከት የህዝቡ አንድነት ከመቸውም ጊዜ በላይ አሁን ላይ ወሳኝነት  አለው ሲሉ የመከላከያ  ውጭ ግንኙነት ዳይሬክተር ብ/ጄነራል ቡልቲ ታደሰ ጠቁመዋል፡፡

(በአመለወርቅ መኳንንት)