ማኅበሩ በትግራይ ክልል በተካሄደው የሕግ ማስከበር ዘመቻ ለተፈናቀሉ ዜጎች ድጋፍ አደረገ

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር (ኢቀመማ) በትግራይ ክልል በተካሄደው የሕግ ማስከበር ዘመቻ ለተፈናቀሉ እና ጉዳት ለደረሰባቸው 2000 ዜጎች ከ3 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ ምግብ ነክ ያልሆኑ ልዩ፣ ልዩ ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል፡፡

ማኅበሩ በትግራይ የተለያዩ አካባቢዎች ካደረገው ድጋፍ መካከል ብርድ ልብስ፣ ምንጣፍ የመመገቢያ እና የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁስ እና መድኃኒት ይገኝበታል፡፡
ኢቀመማ የሕግ ማስከበር ዘመቻውን ተከትሎ ከዓለም ዓቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ እና ከሌሎች ተባባሪ አካላት ጋር በመሆን ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች አስቸኳይ ሠብዓዊ ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱ ይታወቃል፡፡
ድጋፉ የመጀመሪያ ደረጃ የሕክምና እርዳታ፣ የአምቡላንስ አገልግሎት፣ የተጠፋፉ ቤተሰቦችን ማገናኘት፣ የተለያዩ የምግብ እና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁስን እንደሚጨምር ከማህበሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡