ም/ጠ/ሚኒስትሩ ከኬንያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

ኅዳር 21/2015 (ዋልታ) የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከአዲሱ የኬንያ የውጭና የዳያስፖራ ጉዳዮች ሚኒስትር አልፍሬድ ሙቱዋ ጋር በካርቱም ተወያይተዋል።

በሱዳን እየተካሄደ ካለው የኢጋድ ስብሰባ ጎን ሚኒስትሮቹ ባደረጉት ውይይት የሁለትዮሽና የባለብዙ ወገን ወዳጅነቱን ለማጠናከር ተስማምተዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ኬንያ የሰላም ሂደቱ እንዲሳካ እንደ አገር እና በቀድሞ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ላደረገችው አስተዋፅኦ አመስግነው ለስምምነቱ ተፊፃሚነት መንግስት ቁርጠኛ ነው ብለዋል።

የኬንያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አልፍሬድ በበኩላቸው ኬንያ ከኢትዮጵያ ላላት ወዳጅነት የተለየ ቦታ እንደምሰጥና በሰላም ሂደቱ የነበራት ሚና የዚህ ማሳያ እንደሆነ ተናግረዋል።

ሁለቱ አገራት በኢኮኖሚ መስክ በተለይ በንግድና ኢንቨስትመንት መስኮች የተሻለ ትብብር መፍጠር እንደሚችሉም መጥቀሳቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW