ምክር ቤቱ 5ኛ የምርጫ ዘመን 1ኛ አመት የስራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ጉባኤውን ጀመረ

ሐምሌ 29/2013 (ዋልታ) – የሲዳማ ክልል ምክር ቤት አምስተኛ የምርጫ ዘመን አንደኛ አመት የስራ ዘመን ሶስተኛ መደበኛ ጉባኤውን ዛሬ ጀምሯል።

ምክር ቤቱ ለሶስት ቀናት በሚኖረው ቆይታ የ2013 የስራ አፈጻጸም ሪፖርትን የሚገመግም ሲሆን በተጨማሪም የምክር ቤቱን ሪፖርት፣ የፀረ ሙስና ኮሚሽን እና የጠቅላይ ፍርድ ቤት ስራ አፈፃፀምን ይገመግማል ተብሎ ይጠበቃል።

የ2014 የስራ ዘመን የስራ በጀት እቅድ ላይም ይመክራል ተብሎ የሚጠበቀው ምክር ቤቱ በሀገሪቱ ወቅታዊ ጉዳዮች በተለይም የአሸባሪውን የህወሓት ጁንታን እኩይ ድርጊት  አስመልክቶ ምክክር ያደርጋል ተብሏል።

በጉባኤው ላይ የክልሉን ርዕሰ መስተዳደር ጨምሮ ሁሉም የምክር ቤት አባላት ተገኝተዋል።

(በድልአብ ለማ)