ሠራዊታችን ከራሱ በፊት ሕዝብን የሚያስቀድም ነው – ሌተናል ጀኔራል ዘውዱ በላይ

ሚያዝያ 28/2014 (ዋልታ) ሠራዊታችን ከራሱ በፊት ሕዝብን የሚያስቀድም የተቸገሩ ወገኖችን የሚረዳና የሚያግዝ ነው ሲሉ የማዕከላዊ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጀኔራል ዘውዱ በላይ ተናገሩ፡፡
የማዕከላዊ ዕዝ 91ኛ ክፍለ ጦር በአካባቢው ላሉ አቅመ ደካሞች ከ200 ሺሕ ብር በላይ ወጪ በማድረግ የምግብ ነክ ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል።
የክፍለ ጦሩ አባላት ከወር ደመወዛቸው በማዋጣት ነው ድጋፉን ያደረጉት፡፡
በተጨማሪ ለ63 አቅመ ደካማ አባወራዎች እና እማወራዎች የአንድ አመት የጤና መድህን ዋስትና ካርድ መሰጠቱ ተገልጿል።
ሌተናል ጀኔራል ዘውዱ በላይ፤ ሠራዊቱ ወትሮ ዝግጁነቱን የማረጋገጥ ሥራዎችን ከመስራት ጎን ለጎን የተቸገሩ ወገኖችን መደገፍ የሕዝባዊ ባህሪ መገለጫ በመሆኑ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል።
ለሕዝባችን የማንከፍለው ዋጋ የለም ያሉት ሌተናል ጀኔራል ዘውዱ ሠራዊቱ ያደረገው ልዩ ልዩ ድጋፍ የሕዝባዊነቱ መገለጫ ነው።
ድጋፍ የተደረገላቸው አቅመ ደካማ ዜጎች ሠራዊቱ ችግራቸውን ተረድቶ ላደረገላቸው ድጋፍ ማመስገናቸውን ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ነው ያመላከተው፡፡
ለፈጣን መረጃዎች፦
ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth
አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን!