ሩሲያ እና አሜሪካ ለ126ኛው የዓድዋ ድል በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

126ኛው የዓድዋ ድል በዓል

የካቲት 23/2014 (ዋልታ) የሩሲያ እና አሜሪካ ኢምባሲዎች ለ126ኛው የዓድዋ ድል በዓል ለኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ተረክሂን የዓድዋ ድል በዓል የነጻነት ተምሳሌት እና ለአውሮፓ ቅኝ ገዥዎች የአልገዛም ባይ መንፈስን ያወረሰ በመሆኑ ለድሉ በዓል እንኳን አደረሳችሁ ብለዋል፡፡

በዓሉ የኢትዮጵያን አገርነት ያጸና እና በውስጥና በውጭ ፖሊሲዎቿ ጭምር አልበገር ባይነቷን ያሳየ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ድሉ የሁለቱን አገራት ግንኙነት በጠንካራ መሰረት ላይ እንዲፀና መሰረት የጣለ መሆኑም አምባሳደር ተረክሂን አመልክተዋል፡፡

በተመሳሳይ መልኩ በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኢምባሲም በዓሉን አስመልክቶ ለመላው ኢትዮጵያዊያን መልካም ምኞቱን ገልጿል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW