ርዕሰ መስተዳድሩ ከክልሉ የጸጥታ አካላት ጋር ተወያዩ

መጋቢት 26/2014 (ዋልታ) የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ሙሀመድ ከክልሉ የፀጥታ ዓብይ ኮሚቴና ከጅግጅጋ ከተማ አስተዳደር አመራሮች ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም በረመዳን ጾም ወቅት የጅግጅጋ ከተማን ብሎም የክልሉን ሰላም ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም ከረመዳን ጾም ጋር ተያይዞ የእሳት አደጋዎችን አስቀድሞ መከላከል እና የቁጥጥር ሥራዎችን ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መወያየታቸውን ከክልሉ መገናኛ ብዙኃን ኤጀንሲ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡