ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ከክልሉ ልዩ ኃይልና መከላከያ ሠራዊት አባላት ጋር አዲስ ዓመትን አከበሩ

መስከረም 1/2015 (ዋልታ) በሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ሙሃመድ የተመራው የክልሉ ከፍተኛ የመንግስትና የፀጥታ አመራሮች ልዑክ ከክልሉ ልዩ ኃይልና ከመከላከያ ሠራዊት አባላት ጋር አዲስ ዓመትን አከበሩ፡፡

ልዑኩ በኢትዮጵያና በሶማሊያ ድንበር የምትገኘው ኣቶ ከተማ ከሚገኙ የሶማሌ ክልል ልዩ ሀይልና የሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላት ጋር ነው አዲሱን ዓመትን ያከበሩት።

በመርኃ ግብሩ ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሃመድን ጨምሮ ም/ርዕሰ መስተዳድር ኢብራሂም ኡስማንን፣ የክልሉ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አያን አብዲ፣ የሶማሌ ልዩ ኃይልና የሀገር መከላከያ ሠራዊት አዛዦች እንዲሁም ሌሎች አመራሮች ተገኝተዋል።

ልዑኩ ከክልሉ ልዩ ኃይል ሰራዊትና የመከላከያ ሠራዊት አባላት፣ በኣቶ አካባቢ የሚኖሩ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ወጣቶችና እናቶች ጋር መወያየታቸውን የክልሉ ኮሙዩኒኬሽን መረጃ ያመለክታል፡፡

የአካባቢው ነዋሪዎች መንግሥት አከባቢውንና ህዝቡን ከሽብርተኛው የአልሸባብ ታጣቂ ቡድን ለመጠበቅ እየወሰደ ያለው እርምጃዎች እንደሚደግፉና ከሰራዊቱ ጎን እንደሆኑ ገልፀው በአከባቢው የልማት ሥራዎች እንዲሰራላቸው ጠይቀዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ ህዝቡን የልማት ተቋዳሽ ለማድረግ መንግሥት እየሰራ እንደሚገኝ ጠቁመው በሰፍራው ለሚገኘው ሠራዊትም ልዩ ትኩረት እንሰጣለን ብለዋል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW
ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth
ዩቲዩብ https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured
ቲዊተር https://twitter.com/walta_info
አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን!