ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባና የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሽዴ በአፋር የስንዴ ልማትን ጎበኙ

መጋቢት 16/2014 (ዋልታ) የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ እና የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሽዴ በአፋር ክልል ዱብቲ ወረዳ ከ7 ሺሕ ሔክታር በላይ የቆላማ የስንዴ ልማትን ጎብኝተዋል፡፡
የተጎበኘው የስንዴ ልማት በባለሀብት፣ አርብቶ አደር እና ከፊል አርብቶ አደሮች የለማ ሲሆን ለዚህም መንግሥት ከፍተኛ ድጋፍ እያደረገ መሆኑ ተገልጿል፡፡
የክልሉ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት ዘጋበ እንዳመለከተው እንደ አገር በተያዘው አቅጣጫ መሰረት የስንዴ ልማትን በስፋት በማልማት የእርዳታ ስንዴን በማስቀረት በምግብ ራስን ከመቻል ባለፈ የውጭ ምንዛሬን ለማስገኘት በስፋት ሥራ መጀመሩ ይታወቃል፡፡