ርዕሰ መስተዳድር እርስቱ ይርዳ በኮንሶ ዞን የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ሥራ አስጀመሩ

                                                             ርዕሰ መስተዳድር እርስቱ ይርዳ

ጥር 14/2014 (ዋልታ) የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እርስቱ ይርዳ በኮንሶ ዞን የ2014 የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ሥራ በይፋ አስጀመሩ፡፡

በማስጀመሪያ ፕሮግራሙ የደቡብ ብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ጥላሁን ከበደ፣ በግብርና ሚኒስቴር የተፈጥሮ ሀብት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ኢያሱ ኤሊያስ (ፕ/ር)  እና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

በክልሉ 290 ሺሕ 585 ሄክታር መሬት ላይ 3 ሺሕ 103 ንኡስ ተፋሰሶች ተለይተው ለማልማት ታቅዷል።

ከክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ እንዳመለከተው የዘንድሮውን የተፋሰስ ልማት ሥራ ባለፉት ዓመታት የታዩ ምርጥ ተሞክሮን መነሻ በማድረግ የአፈር እና ጥበቃ ሥራውን ስኬታማ ለማድረግ እንደሚሰራ ተጠቁሟል።