ሰላም እና አካቶ ትምህርት ላይ ያተኮረ ኮንፈረስ ተካሄደ

ጥር 21/2014 (ዋልታ) በሀራምቤ ዩኒቨርሲቲ ሰላም እና አካቶ ትምህርት ላይ ያተኮረ ኮንፈረስ ተከሄደ::

ኢትዮጵያ የገጠማትን ችግር በአገራዊ ምክክር ለመፍታት እየተሰራ ባለበት በዚህ ወቅት እንዲህ አይነት የምክክር ኮንፈረሶች የላቀ ፍይዳ እንዳላቸው የዩኒቨርስቲው ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፈይሳ አራርሳ ገልፀዋል::

የፓን አፍሪካኒዝም አቀንቃኝ የሆነው ሀራምቤ ዩኒቨርሲቲ የአፍሪካ ሰላም እና ወንድማማችነት ላይ የጀመረውን ሥራ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ገልፀዋል።

በመድረኩ ላይ የተገኙት የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፍ ገላና ወ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሰላም ፅንሰ ሀሳብን በመረዳት ለሰላም ሁሉም የበከሉን አስተዋፅኦ ሊወጣ ይገባል ብለዋል።

ለዚህም ህፃናት ገና ከልጅነታቸው ጀምረው የሰላም እሴትን እንዲረዱ በክልሉ የገዳ ሥርዓትን በትምህርት ካሪኩለሙ ውስጥ በማካተት ትምህርት እየተሰጠ መሆኑን ገልፀዋል።

በኮንፈረሱ ላይ ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የተውጣጡ ምሁራን በሰላም እና አካቶ ትምህርት ላይ ጥናት አቅርበው ውይይት ተደርጎበታል።
በአሳየናቸው ክፍሌ