ሰላምና ብልጽግናን ለማረጋገጥ ጦርነትን ማስቀጠል የለብንም – ጠ/ሚ ዐቢይ

ኅዳር 6/2015 (ዋልታ) ሰላምና ብልጽግናን ለማረጋገጥ ጦርነትን ማስቀጠል የለብንም ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ፡፡
የሰላም መጥፎ የጦርነት መልካም የለውም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ እያሽነፍንም ቢሆን ከጦርነት ኪሳራ እንጂ ትርፍ አይገኝም ብለዋል፡፡
ንግግርና ውይይትም ካለ ለኢትዮጵያ አንድነት ብቻ ነው የምናደርገው ሲሉ ገልጸዋል፡፡
በየቀኑ ከሰላም ማትረፍ ስለምንችል ሰላም ለማምጣት አስፈላጊውን ሁሉ እናደርጋለን ብለዋል፡፡
ሰላም ሲባል ጦርነት ማቆም ብቻ ሳይሆን ሕግ ማስከበረም ጭምር ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሀገሪቱ ውስብስብ ችግር ያለባት ብትሆንም ጦርነት በማቆም እና በመነጋገር ችግሮቻችንን እንፈታለን ብለዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለግጭት ምክንያት በሆኑ የድንበር ወሰን ይገባኛል ጥያቄ ያለባቸውን አካባቢዎች አስመልክቶ በሰጡት ማብራሪያ በቀጣይ በሀገራዊ ልምምድ ችግሮችን በመነጋገር መፍታት እንደሚቻል ገልጸዋል፡፡
በብርሃኑ አበራ