ሰበር ዜና ፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጦርነቱ በከፍተኛ ድል እየተካሄደ ነው አሉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ

ኅዳር 17/2014 (ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሚገኙበት ግንባር መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

የሰራዊቱ ሞራል እጅግ ደስ ይላል ጦርነቱ በከፍተኛ ድል ነው እየተካሄደ ያለው ብለዋል፡፡

ጠላት ከእኛ ጋር የሚያፎካክር አቅም የሌውም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጠላት እስከትናንት ይዞት የነበረውን ቦታ አስለቅቀን ካሳጊታን ይዘናል ዛሬ ጭፍራንና ቡርቃን እንይዛለን ብለዋል፡፡

የኢትዮጰያ ነፃነት እስኪረጋገጥ ወደ ኋላ አንልም የምንፈልገው እኛ ሞተን የምትኮሩ ኢትዮጵያዊያንን ማስቀጠል ነው ብለዋል፡፡

ነገም ይቀጥላል ታላለቅ ድሎች ይኖራሉ ነው ያሉት፡፡