ነሀሴ 06/2013 (ዋልታ) – በኳታር ብረታ ብረት በማምረት እና ባትሪን መልሶ ጥቅም ላይ በማዋል የሚታወቀው የሳሄል ሆልዲንግ ግሩፕ ለታላቁ የኢትዮጵያ የሕዳሴ ግድብ 10 ሺህ የአሜሪካን ዶላር ድጋፍ አድርጓል።
ድጋፉንም የኩባንያው የቢዝነስ ልማት ዳይሬክተር ዶ/ር ሃሰን አልሳማዲ በኳታር የኢትዮጵያ ሚሲዮን ተገኝተው ለአምባሳደር ሳሚያ ዘካሪያ አስረክበዋል።
ኩባንያው በአሁኑ ወቅት በደብረ ብርሃን ከተማ መሬት ተረክቦ ባትሪን መልሶ ጥቅም ላይ በማዋል እና በማቀነባበር ላይ የሚሰራ ፋብሪካ በመገንባት ላይ ይገኛል።
ሳሄል ሆልዲንግ ግሩፕ በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት ስራውን እንዲጀምር ኤምባሲው ለሰጠው እና እያደረገለት ለሚገኘው ድጋፍ የኩባንያው ዋና ስራ አስኪያጅ ሚስተር ዚያድ ኤሳ የምስጋና ደብዳቤም ማቅረባቸው ታውቋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል::