ሳማሪታን ፐርስ አዳዲስ የሕክምና መሳሪያዎችና የሕክምና ቁሳቁስ ወደ ኢትዮጵያ ላከ

የካቲት 9/2014 (ዋልታ) ሳማሪታን ፐርስ የተባለው የአሜሪካ ዓለም ዐቀፍ የረድኤት ድርጅት በጦርነቱ የተጎዱና የተዘረፉ የሕክምና ግብዓቶችን ለመተካት የሚያስችሉ አዳዲስ የሕክምና መሳሪያዎች እና የሕክምና መገልገያ ቁሳቁስ ወደ ኢትዮጵያ መላኩን በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍፁም አረጋ አስታወቁ።

አምባሳደር ፍፁም በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው እርዳታውን በማመቻቸት በአውሮፕላን በነጻ ወደ ኢትዮጵያ እንዲጓጓዝ ላደረጉት የቢሊ ግርሃም ቤተሰቦች በተለይም ለድርጅቱ ፕሬዝዳንት ፍራንክሊን ግራሃም እና ልጃቸው ኤድዋርድ ግራሃም እንዲሁም በእርዳታው ለተሳተፉ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።