ሳይበርን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶችን መመከት ይገባል – ብርሀኑ ነጋ (ፕ/ር)

ጥቅምት 01/2014 (ዋልታ) ሳይበርን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶችን መመከት እንደሚገባ የትምህርት ሚኒስትር ብርሀኑ ነጋ (ፕ/ር) አሳሰቡ፡፡

“የሳይበር ምህዳሩን ተጠንቅቀን እንጠቀም” በሚል መሪ ሀሳብ 2ኛው ብሔራዊ የሳይበር ደህንነት ወር እየተከበረ ይገኛል።

በስነ ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሀኑ ነጋ (ፕ/ር) ሳይበርን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች ለመመከት የሳይበር ደህንነት መዋቅር መገንባት፣ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን መስራት እና የሳይበር ጥቃቶች መመከት እንደሚገባ ተናግረዋል።

የሳይበር ደህንነት ለማረጋገጥ ህጎችንና ደህንነቶችን ማስተዋወቅና ዜጎች ለሳይበር ደህንነት የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ ማድረግ ተገቢነት እንዳላቸው ተጠቅሷል።

በሀገሪቱ የሳይበር ደህንነትን ለማስጠበቅ በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ሊሰጥ እንደሚገባውም ተነስቷል፡፡

የሳይበር ጥቃት በኢትዮጵያ በ2013 ዓ.ም የተሰነዘረው ጥቃት ከ2012 ዓ.ም ጋር ሲነፃፀር ጥቃቱ በእጥፍ መጨመሩም ተነግሯል።

በዙፋን አምባቸው