ስለ ኢትዮጵያ የተሰኘ የፎቶ ግራፍ አውደ ርዕይ  ለእይታ በቃ

ስለ ኢትዮጵያ የተሰኘ የፎቶ ግራፍ አውደ ርዕይ

ታኅሣሥ 25/2014 (ዋልታ) ስለ ኢትዮጵያ በሚል ርዕስ የተዘጋጀው የፎቶ ግራፍ አውደ ርዕይ በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ለእይታ በቃ።

አውደ ርዕዩ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿ አገርን ለማዳን ያደረጉትን ተጋድሎ የሚያሳይ ሲሆን  ድርጅቱ ላለፈው አንድ ዓመት ከሁለት ወር በዘለቀው ጦርነት የነበሩ ኹነቶችን በፎቶ ሰንዶ ያስቀመጣቸው እንደሆነ ተመላክቷል።

በአውደ ርዕዩ በትግራይ ክልል የአገር መከላከያ ሰራዊት ሰሜን ዕዝ ከሕዝቡ ጋር የነበረው መስተጋብርና ያበረከተው አስተዋጽኦ፣ የደረሰበት ጥቃትና ጉዳት የሚያሳዩ ፎቶዎች መሆናቸውም ተጠቁሟል።

የሀገር መከላከያ ሰራዊት አገርን ለማዳን የከፈለውን መስዋዕትነት የሚያሳዩ ፎቶዎች በአውደ ርዕዩ ላይ ለጎብኝዎች ክፍት ተደርገዋል።

የሕወሓት ቡድን በአማራና አፋር ክልሎች ፈጽሞት በነበረው ወረራ በዜጎች ላይ ያደረሰውን አሰቃቂ ድርጊቶችና በተለያዩ ተቋማት ላይ ያደረሰውን ከፍተኛ ውድመትና ዝርፊያ የሚያሳዩ ፎቶዎች በአውደ ርዕይው ተካቷል።

አውድ ርዕዩ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ጥር 12 ቀን 2014 ዓ.ም እንደሚቆይም ታውቋል፡፡

በዙፋን አምባቸው