ስልጤ ዞን ከ13 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ ለሰራዊቱ ለገሰ

ጥቅምት 30/2014 (ዋልታ) የስልጤ ዞን ማህበረሰብ ከ13 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የሰንጋ በሬ እና ሙክት ለመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ አደረገ።

የስልጤ ዞን ማህበረሰብ ለ4ኛ ዙር ለአገር መከላከያ ሰራዊት ድጋፍ ባደረገበት ወቅት በስፍራው ተገኝተው ድጋፉን የተቀበሉት የመከላከያ ሚኒስትር ዴኤታ ማርታ ሉዊጂ ድጋፉ አሸባሪውን ቡድን ከአገር ለማጥፋት በሚደረገው ጥረት የስልጤ ዞን ከሰራዊቱ ጎን መቆሙን ማሳያ ነው ብለዋል።

የስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አሊ ከድር ድጋፉ የማይቋረጥ እና ቀጣይነት የሚኖረው መሆኑን ገልጸዋል፡፡