ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ለዓይነስውራን እየተገነባ ያለው አዳሪ ት/ቤት ጎበኙ

ጥቅምት 22/2014 (ዋልታ) ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በጽሕፈት ቤታቸው እየተገነቡ ካሉት ውስጥ የሆነውን የዓይነስውራን አዳሪ ትምህርት ቤት ጎበኙ፡፡

ጽሕፈት ቤቱ በ400 ሚሊዮን ብር የሚያስገነባው ትምህርት ቤት 320 ዓይነስውራንን ማስተናገድ የሚችል ሲሆን ለዓይነስውራኑ በሚመች መልኩ እየተገነባ ነው፡፡

አዳሪ ትምህርት ቤቱ የተማሪዎችን መኖሪያ፣ የአስተዳደር ህንፃ፣ የአስተማሪዎች መኖሪያ፣ የእንግዳ ማረፊያ፣ ቤተ መጻሕፍት፣ የመመገቢያ አዳራሽ እና የኮምፒውተር ቤተ ሙከራ ያሟላ እንደሆነ ከቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡