በ11 ቀናት ውስጥ ከ4 ሺሕ 900 በላይ ዜጎች ከሳኡዲ አረቢያ መመለሳቸው ተገለጸ

መጋቢት 30/2014 (ዋልታ) ዜጎችን ከሳኡዲ አረቢያ ወደ ኢትዮጵያ የመመለሱ ሥራ ተጠናክሮ መቀጠሉን የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በዚህም በዛሬው ዕለት ከገባው የመጀመሪያው በረራ 101 ህጻናት ወደ ሀገራቸው መመለሳቸው ተጠቁሟል፡፡

መንግሥት ዜጎችን ወደ ሀገር በመመለስ የተለያዩ ድጋፎችን እንዲያገኙ እያደረገ እንደሚገኝም የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል፡፡

የመመለሱ ሥራ እስካሁን አስራ አንደኛ ቀኑን የያዘ ሲሆን ከ4 ሺሕ 900 በላይ ዜጎችን ለመመለስ እንደተቻለም ተመላክቷል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW