በ2014 የኢትዮጵያ ውኃ ዋና ሻምፒዮና አማራ ክልል አሸናፊ ሆነ

ሚያዝያ 7/2014 (ዋልታ) በ2014 ዓ.ም የኢትዮጵያ ውኃ ዋና ሻምፒዮና አማራ ክልል በሁለቱም ፆታ አሸናፊ ሆኗል።

ከሚያዝያ 01/2014 ዓ.ም ጀምሮ በቢሾፍቱ ከተማ አስተናጋጅነት ሲካሄድ የነበረው የ2014 የኢትዮጵያ ውኃ ዋና ሻምፒዮና ዛሬ ተጠናቋል።

የአማራ ክልል በሁለቱም ፆታ አጠቃላይ አሸናፊ ሆኖ ሁለቱንም ዋንጫዎች ሲወስድ ክልሉ ለስፖርቱ ባበረከተው አስተዋፅኦ ልዩ የዋንጫ ተሸላሚ ሆኗል።

ኦሮሚያ ፖሊስ የውሃ ዋና ክለብ የፀባይ ዋንጫ ተሸላሚ ሲሆን በወንዶች ጥላሁን አያል ከአማራ ክልል የሻምፒዮናው ኮኮብ ተጫዋች ተብሏል።

ብርሃን ደመቀ ደግሞ በሴቶች ከዳዊት እምሩ ኮንስትራክሽን ተቋራጭ ክለብ ኮኮብ ተብላለች።

ኮከብ አሰልጣኝ ማንደፍሮ ተገኝ ከአማራ ክልል ሆኖ ተመርጧል።

የኢትዮጵያ ውኃ ስፖርቶች ፌዴሬሽን ውድድሩ ተተኪዎች የታዩበትና በቀጣይም በአፍሪካና ዓለም ዐቀፍ ውድድሮች አገሪቱን የሚወክሉ ስፖርተኞች አቅም የታየበት መሆኑን ገልጿል፡፡

ደግነት መኩሪያ (ከቢሾፍቱ)