በ3 ሺህ የወንዶች መሰናክል ኢትዮጵያኖች 2ኛና 4ኛ ደረጃን ያዙ

ሐምሌ 26/2013 (ዋልታ) – በሶስት ሺህ የወንዶች መሰናክል የፍጻሜ ውድድር ኢትዮጵያኖች ሁለተኛ እና አራተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀቁ፡፡

በውድድሩ ኢትዮጵያዊ አትሌት ላሜቻ ግርማ ሁለተኛ  ሆኖ በማጠናቀቅ ለኢትዮጵያ የብር መዳሊያ አስገኝቷል፡፡

ጓደኛው ጌትነት ዋለ ደግሞ አራተኛ በመውጣት ውድድሩን አጠናቋል።