በ5 ወራት ብቻ 1 ቢሊየን 356 ሚሊየን 119 ሺህ ብር የሚገመቱ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ተይዘዋል

የንግድ ውድድሩን ፍትሃዊ ለማድረግና የኮንትሮባንድ እንቅስቃሴን ለመቆጣጠር የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽን ባደረጉት ክትትል ባለፉት አምስት ወራት ብቻ 1 ቢሊየን 356 ሚሊየን 119 ሺህ ብር የሚገመቱ ወጪና ገቢ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች መያዛቸውን ከገቢዎች ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ አመልክቷል፡፡

ከዚህ ውስጥ 1 ቢሊየን 100 ሚሊየን 631 ሺህ ብር የሚገመት ገቢ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ሲሆኑ ቀሪዎቹ ወጪ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ናቸው፡፡

የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹን ለመያዝ ቀን ከሌት በመስራት ትልቅ አስተዋፅኦ ላበረከቱ የጉምሩክ ኮሚሽን፣ የጉምሩክ ኬላ እና መቆጣጠርያ ጣቢያ አመራርና ሠራተኞች እንዲሁም የአገር መከላከያ ሠራዊት አባላት፣ የፌደራልና የክልል የፀጥታ አካላትና ጥቆማ በመስጠት ለተባበሩ ሁሉ ሚኒስቴሩ ምስጋና አቅርቧል፡፡

በቀጣይ ወራትም ህገ ወጥ ንግድና ኮንትሮባንድን በመከላከል የንግድ ውድድሩን ፍትሀዊ ለማድረግ የገቢዎች ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት የተጠናከረና የተቀናጀ ስራ እንደሚሰሩ ተገልጿል፡፡