ሐምሌ 11/2013 (ዋልታ) – በሀረሪ ክልል ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ከ14 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ ተሰበሰበ።
የታላቁ ህዳሴ ግድብ ዋንጫ በሀረሪ ክልል የነበረውን ቆይታ አጠናቆ ወደ ድሬዳዋ አስተዳደር ተሸኝቷል።
በስነስርአቱ ላይ የተገኙት የክልሉ ምክት ርዕሰ መስተዳድር እና በክልሉ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ም/ቤት ሰብሳቢ ወ/ሮ ሚስራ አብደላ እንደተናገሩት ታላቁ ህዝቡ የኑሮ ደረጃና ዕድሜ ሳይገድበው ለግድቡ ግንባታ አሻራ በማኖር የማይቻል የሚመስለውን እንደምንችል ለዓለም ያሳየንበት ፕሮጀክት ነው ብለዋል።
ታላቁ ህዳሴ ግድብ ዋንጫ ባለፉት ወራት በክልሉ በነበረው ቆይታ በ9 ወረዳዎች፣ ተቋማት፣ ትምህርት ቤቶች እና እና ሌሎች አካባቢዎች በማዟዟር ድጋፍ ከማሰባሰብ ባለፈ የህብረተሰቡን ግንዛቤን የማስፋት ስራ በትኩረት ሲከናወን ቆይቷል ብለዋል።
ከገቢ አንፃርም በክልሉ በነበረው የአምስት ወራት ቆይታ ከ14 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ ከቦንድ ሽያጭ መሰብሰቡ ተችሏል፡፡
በእለቱ ከገቢ አሰባሰብ ጋር ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ወረዳዎች እና ተቋማት እንዲሁም ባለሀብቶች የእውቅና አሰጣጥ ስነስርዓት መካሄዱን ከሀረሪ መንግስት ኮሚዮኒኬሽን ጉዳዮች ቦሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።