በሀረሪ ክልል የ10 ኪ.ሜ ሩጫ ውድድር ተካሄደ

የሰላም ቀን የሩጫ ውድድር

ጳጉሜ 3/2014 (ዋልታ) በሀረሪ ክልል ጳጉሜ 3 የሰላም ቀንን ምክንያት “ሰላም ለኢትዮጵያ በማድረግ” በሚል መሪ ቃል የ10 ኪሎ ሜትር የሩጫ ውድድር ተካሄደ።

መነሻና መድረሻው ኢማም አህመድ ስታዲየም በተደረገው የሩጫ ውድድር ከ1ኛ እስከ 3ኛ ላጠናቀቁ ተወዳዳሪዎች ከክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ የሜዳሊያ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

ስፖርት ሰላምን ለማጠናከር ያለው ሚና የጎላ በመሆኑ የሰላም ቀንን በተለያዩ ስፖርታዊ ውድድሮች ለማክበር የሩጫ ውድድሩን ማዘጋጀት አስፈላጊ ሆኖ መገኘቱ ተገልጿል።

በውድድሩ የተሳተፉ ዜጎች በሰላም ቀን በተካሄደው ውድድር ላይ በመሳተፋቸው መደሰታቸውን ገልፀው ለመሠል በጎ ዓላማ የሚካሄዱ ስፖርታዊ ውድድሮች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል።

ከዚህ በተጨማሪም የሰላምን መልዕክት ያዘለ የሰላም ፖል የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ በተገኙበት ተተክሏል፡፡

በተስፋዬ ኃይሉ

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW