በሀረሪ ክልል የብልጽግና ፓርቲ ውሳኔዎቸና አቋሞች ላይ የሕዝብ የውይይት ሊደረግ ነው

መጋቢት 12/014 (ዋልታ) ብልጽግና ፓርቲ በቅርቡ ባካሄደው የመጀመሪያ ጉባኤ በመከረባቸው ውሳኔዎቸና አቋሞች ላይ የሚመክሩ የሕዝብ የውይይት መድረኮች ከመጋቢት 14 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚካሄድ የሀረሪ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ገለጸ።

የጽሕፍቱ ቤት ኃላፊ አብዱጀባር መሀመድ እንደገለጹት መድረኩ የብልጽግና ፓርቲ ጉባኤ የመከረባቸው መሠረታዊ ጉዳዮችን ሕዝቡ እንዲገነዘባቸውና እንዲያዳብራቸው ያስችላል።

በጉባኤው በተላለፉ ውሳኔዎች ተፈፃሚነት የክልሉ ሕዝቡ የበኩሉን ሚና እንዲጫወት መድረኩ ያግዛልም ነው ያሉት።

ከሕዝቡ የሚነሱ ሃሳቦችን በመውሰድ በቀጣይ ፓርቲው የሚሰራቸውን ሥራዎች አቅጣጫ ለማስቀመጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ጠቁመዋል።

ከሕዝብ ጋር የሚካሄዱ የውይይት መድረኮችን በጉባኤው የተመረጡ የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት፣ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላትና በየደረጃው ያሉ አመራሮች የሚመሩት መሆኑን የክልሉ መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን መረጃ አመላክቷል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth
አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን!