በሀገር አቀፍ ደረጃ የተጠናው የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ጥናት ይፋ ሆነ

                              አቶ ገዛኸኝ መኮንን

መጋቢት 01/2013 (ዋልታ) – በሀገር አቀፍ ደረጃ የተጠናው የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ጥናት በዛሬው ዕለት ይፋ ሆኗል፡፡

ጥናቱም በዋናነት የህግ ማእቀፍ ክፍተቶች፣ የልደት የፍቺ እና መሰል ነጥቦች ላይ ትኩረት ያደረገ ነው ተብሏል፡፡

የኢምግሬሽንና ወሳኝ ኩነት ጥናት ምርምርና አሰራር ስርዓት ማሻሻያ ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ መኮንን በጥናቱ መሰረት የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ዙሪያ ማህበረሰቡ ያለው እውቀት አናሳ መሆኑን ጠቁመው፣ ይህ ጥናት መደረጉ በቀጣይ በጥናቱ የተስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት እና ጥንካሬዎችን ለማስቀጠል ያግዛል ብለዋል፡፡

ምንም እንኳን ኢትዮጵያ ከአፍሪካ በህዝብ ብዛት ሁለተኛ ብትሆንም ይህን ማህበረሰብ በወሳኝ ኩነት ምዝገባ አሰራር ስር የማካተት ተግባራት የተዳከመ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

የማህበረሰቡን ግንዛቤ ለማሻሻል ከኃይማኖት ተቋማት፣ ከመገናኛ ብዙሀን ብሎም ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት መስራት እንደሚያስፈልግም ገልጸዋል፡፡

በ2008 ዓ.ም የተጀመረው ጥናቱ የነዋሪዎች የዲጅታል መታወቂያ ምዝገባ፣ የፍቺ ምዝገባ እንዲሁም የሞት መንስኤ ምዝገባ አለመኖሩን አመላክቷል፡፡

(በሄብሮን ዋልታው)