በሁለተኛው ዙር በረራ ከሳዑዲ አረቢያ 354 ዜጎች ተመለሱ

ሚያዝያ 10/2014 (ዋልታ) ዛሬ ከጂዳ በተደረገው ሁለተኛ በረራ 354 ዜጎች ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃልአቀባይ ጽሕፈት ቤት አስታወቀ።

ተመላሾች ሁሉም ወንዶች ሲሆኑ አዲስ አበባ ሲገቡ የሚኒስቴሩ ሰራተኞች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

በዛሬው ዕለት የመጀመሪያ በረራ 348 ዜጎች ከሳዑዲ አረቢያ ወደ ኢትዮጵያ መመለሳቸውን መዘገባችን የሚታወስ ነው፡፡

መንግሥት በሳዑዲ አረቢያ በአስከፊ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሚመራና 16 መንግሥታዊ መስሪያ ቤቶችን በአባልነት ያቀፈ ብሔራዊ ኮሚቴ በማዋቀር 102 ሺሕ ዜጎችን ወደ ሃገር ለመመለስ በማቀድ ወደ ሥራ መግባቱ ይታወሳል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW