በህወሐት አመራሮችና አርቲስቶች መካከል ውዝግብ መፈጠሩ ተገለጸ

ሐምሌ 24/2013 (ዋልታ) – ህወሐት የገጠመውን የፋይናንስና የሎጅስቲኪ ችግሮችን ለመቅረፍ ታስቦ ሱዳን በሚገኙ ስደተኞች ሽፋን ሊካሄድ የተዘጋጀው የገቢ ማስገኛ የሙዚቃ ዝግጅት ገንዘቡን ማን ያድርስ በሚለው ጉዳይ ላይ ከፍተኛ አመራሮቹና አርቲስቶቹ መካከል ውዝግብ መፈጠሩን የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የውስጥ አዋቂ ምንጮች አስታወቁ።

ሽብርተኛው ህወሐት አሁን ላይ የገጠመውን ችግሮችን ለመፍታት የተለያዩ አማራጮችን ለመጠቀም ጥረት በማድረግ ላይ ነው፡፡

ህዝባዊ ወያነ ሐርነት ትግራይ (ህወሐት) በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አሸባሪ ጸብሎ መሰየሙ ይታወሳል፡፡

አሸባሪው ህወሓት የሽብር ቡድኑ ሀምሌ 23 ቀን 2013 ዓ.ም በሱዳን ለሚገኙ የትግራይ ስደተኞች የገቢ ማስባሰቢያ መርሃ ግብር በሚል ሽፋን ከተለያዩ ዓለማት በመጡ የጁንታው ደጋፊ ሙዚቀኞች አማካኝነት በካርቱም ቡሪ በተባለ አካባቢ በሚገኝ አንድ ሆቴል ውስጥ ከምሽቱ አንድ ሰአት ጀምሮ ፕሮግራም ማካሄዱ ተሰምቷል፡፡

በዚህም ፕሮግራም ላይ በሺዎች የሚቆጠሩ ደጋፊዎቹና ተባባሪዎቹ ተገኝተዋል ተብሏል፡፡

ከዝግጅቱም በሰው እስክ 10ሺህ የሱዳን ፓውንድ እንደተሰበሰብ ይጠበቃል ያሉት ምንጮቻችን፤  ለትግራይ ህዝብና እና እናቶች ደንታ የሌላቸው የስግብግቡ ጁንታው ከፍተኛ አመራሮች የለመዱትን የጫካውን አይነት ጭካኔ በመፈፀም ከዝግጅቱ የሚገኘውን የገንዘብ ገቢ ወደ ግል ኪሳቸው ለማስገባት ቋምጠዋል ተብሏል።

የሙዚቀኞች ቡድን የሚሰበሰበውን ገንዘብ እኛ እራሳችን ለስደተኞች በአካል ተገኝተን እናደርሳልን በሚል የጁንታውን ከፍተኛ አመራሮች እየሞገቱ ሲሆን፤ የሽብርተኛው አመራሮች በበኩላቸው ገንዘቡን ለራሳቸው ጥቅም ለማዋል ባላቸው ፍላጎት ከሙዚቀኞች ቡድን ጋር ግብግብ ፈጥረዋል ተብሏል፡፡

በመሆኑም የሽብር ቡድኑ በትግራይ ህዝብ ስም የሚገኝን ገንዘብ ለጦርነት ዓላማው እየተጠቀመበት ሲሆን፤ በአስከፊ ችግርና መከራ ውስጥ ያለው የትግራይ ህዝብ የአሸባሪውን የህወሃት ቡድንን እኩይ ድርጊት ሊቃወመውና ተው ሊለው ይገባል ካሉ በኃላ፤ በተጨማሪም በሱዳን እየታየ ያለው ውስጣዊ የሰላም እጦትና ችግር ላይ ተመስርቶ ለጁንታው ጥላቻ ያላቸው ማንነታቸው የማይታወቅ አካላት ጥቃት ሊፈጽሙ እንደሚችሉም ጭምር ውስጥ አዋቂ ምንጮቻችን ያላቸውን ስጋት አሳውቀዋል  ሲል የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዘግቧል፡፡