በህዳሴ ግድቡ ዙሪያ የተጀመረውን ውይይት ለማስቀጠል ስምምነት ላይ ተደረሰ

የኢትዮጵያ እና ሱዳን የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስተሮች በህዳሴ ግድቡ ዙሪያ በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት የተጀመረውን ውይይት ለማስቀጠል ተስማምተዋል፡፡

የውሃ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ኢንጅነር ስለሺ በቀለ ከሱዳኑ አቻቸው ፕሮፌሰር ያሲር አባስ ጋር ትናንት በኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ በሚደረገው ሶስትዮሽ ድርድር ውይይት አድርገዋል፡፡

ሁለቱ ወገኖች ድርድሩን ተስማምተው ለማስቀጠል እና ክፍተቶች እንዳይፈጠሩ ለማድረግ የአፍሪካ ህብረት የባለሙያዎች ቡድን በድርድሩ ሂደት ላይ ትልቅ ሚና እንዲኖረው ስምምነት ላይ መደረሱ ተገልጿል፡፡

ዶክተር ስለሺ በቀለ ከሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክ ጋር ውይይት ማድረጋቸውን የሱዳን መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል፡፡