በህገ-ወጥ መንገድ ሕፃናትን ሲያዘዋውር የተገኘው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ

ግንቦት 4/2014 (ዋልታ) በህገ-ወጥ መንገድ ሰባት ሕፃናትን ሲያዘዋውር የተገኘው ግለሰብ ቁጥጥር ስር መዋሉን የቤንች ሸኮ ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ።
የዞኑ ፖሊስ እንዳስታወቀው ተጠርጣሪው ግለሰብ ከካፋ ዞን ጨና ወረዳ ባላ ሻሻ ቀበሌ ከአስር ዓመት በታች የሆኑ ሰባት ሕፃናትን ከሚኖሩበት ቤተሰብ ከብቶችን ትጠብቃላችሁ በማለት ወደ ቤንች ሸኮ ዞን ሸኮ ወረዳ ጉፍቃ ቀበሌ ግንቦት 1 ቀን 2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00 በተሽከርካሪ ይዞ በመጓዝ ላይ እንዳለ ከኅብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ሆኖ ምርመራ እየተደረገበት ይገኛል።
ፖሊስ ኅብረተሰቡ ህፃናቶች በህገወጥ መንገድ ከቦታ ወደ ቦታ እያዘዋወሩ ለጉልበት ብዝበዛ የሚዳርጉ ግለሰቦችን ለህግ አካላት አሳልፎ መስጠት እንዳለበትም ማሳሰቡን ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።