በልደታ ክፍለ ከተማ የሚገኙ የትግራይ ተወላጆች በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ዙሪያ እየተወያዩ ነው

ነሃሴ 25/2013 (ዋልታ) – በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ዙሪያ በልደታ ክፍለ ከተማ የሚገኙ የትግራይ ተወላጆች እየተወያዩ ይገኛሉ፡፡

ውይይቱ በወቅታዊ ሀገራዊ ሁኔታና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን ያደረገ ሲሆን፣ ኢትዮጵያ ከውስጥና ከውጭ የገጠማትን ፈተና በሚመለከት የውይይት ሰነድ ቀርቧል፡፡

በአትዮጵያ ላይ ከውስጥ ባንዳ ከውጭ ባዕዳን እየደረሰ የሚገኘውን ጫና ለመግታት የትግራይ ተወላጆች ሚናቸውን እንዲወጡ ተጠይቋል፡፡

በመሆኑም ትህነግን ባለመተባበርና በማጋለጥ ረገድ በአዲስ አበባ የሚገኙ የትግራይ ተወላጆች ሚና ከፍተኛና የሚጠበቅ ነው ተብሏል፡፡

በተጨማሪም ህገ ወጥ ተግባራትን በመከላከልና በማጋለጥ በኩል ተሳትፏቸውን ተወላጆቹ ማጠናከር እንደሚገባቸው ተነስቷል፡፡

(በሰለሞን በየነ)