በሐይቅ ከተማ 3 ሺሕ ገደማ የብሬንና ክላሽ ጥይት መያዝ

ጳጉሜ 4/2013 (ዋልታ) በሐይቅ ከተማ አስተዳደር በሕገ ወጥ መንገድ ሊዘዋወር የነበረ የብሬን እና የክላሽ ጥይት እና 4 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የሐይቅ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽሕፈት ቤት አስታወቀ።

የከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ኮማንደር ጌታቸው ሙላቱ እንደገለጹት በሐይቅ ከተማ አስተዳደር 01 ቀበሌ ልዩ ስሙ ሸሕ ሙሳ በሚባለው አካባቢ ወደ 2 ሺሕ 451 የክላሽን ጥይት እና 360 የብሬን ጥይት ለግብይት ሊዘዋወር ሲል በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡

በወንጀል ድርጊቱ የተጠረጠሩ 4 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው በመጣራት ላይ ነውም ተብሏል፡፡