በሕገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀስ የነበር 12 ሺሕ ሊትር ነዳጅ ተያዘ

ሚያዝያ 3/2014 (ዋልታ) በሕገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀስ የነበር ከ12 ሺሕ ሊትር በላይ ነዳጅ መያዙን የሰሜን ጎንደር ዞን አስታወቀ፡፡

ሕገ ወጥ የንግድ ሥርዓትን ለመከላከል ዞኑ ለአንድ ወር ያክል በሰራው የቁጥር ሥራ ከ7 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው የኢንዱስትሪ ውጤቶችና የግብርና ምርቶች በቁጥጥር ስር ማዋሉ ተገልጿል።

ምርቶቹ የተያዙት የዞን አሥተዳደሩ ጥምር ኃይል አቋቁሞ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ በቤት ለቤት አሰሳና በኬላዎች ላይ ባደረገው ድንገተኛ ፍተሻ መሆኑም ተመላክቷል።

41 ተጠርጣሪዎችም በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የአሚኮ ዘገባ ያመለክታል፡፡

በንግድ ሥርዓቱ ላይ ሰው ሰራሽ ችግር ሲፈጥሩ በተገኙ 320 ድርጅቶች ላይም ሕጋዊ እርምጃ ተወስዷል ነው የተባለው።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW