በመተከል ከ42 ሺሕ ኩንታል በላይ ሰብዓዊ ድጋፍ ለተፈናቃዮች እየተሰራጨ ነው


ሚያዝያ 4/2014 (ዋልታ)
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን በተለያዩ መጠለያ ጣቢዎች ለሚገኙ ተፈናቃዮች 5ኛው ዙር ሰብዓዊ ድጋፍ በመቅረብ ላይ መሆኑን የክልሉ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
በዞኑ በተፈጠረው አለመረጋጋት ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ዜጎች የሚቀርበው ሰዓብዊ ድጋፍ በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገልጿል።
ኮሚሽኑ ከብሔራዊ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ጋር በመተባበር ከ42 ሺሕ 300 ኩንታል በላይ ሰብዓዊ ድጋፍ በመጠየቅ በአሁኑ ሰዓት ለተፈናቃዮች እያቀረበ መሆኑን በኮሚሽኑ የምላሽ ፍላጎትና እርዳታ ከፍተኛ ባለሙያ ዘውዱ ተሾመ አስታውቀዋል።
በአሁኑ ወቅት በዞኑ ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ 282 ሺሕ የኅብረተሰብ ክፍሎች በየወረዳው ባሉ መጠለያ ጣቢያዎች እንደሚገኙ ከመተከል ዞን ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።