በመተከል ዞን እየተከሰተ ያለውን ችግር ከመሰረቱ ለማጥፋት በህብረትና በትኩረት መስራት ያስፈልጋል – ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን  እየተከሰተ ያለውን  ችግር  ከመሰረቱ ለማጥፋት በህብረት  እና  በትኩረት  መስራት እንደሚጠይቅ ጠቅላይ  ሚኒስትር  ዐቢይ አህመድ ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቤኒሻንጉል ክልል መተከል ውስጥ በዜጎች ላይ እየተፈጸመ ያለው ጭፍጨፋ እጅግ አሳዛኝ ሆኗል ያሉ ሲሆን፣ በወገኖቻችን ላይ በተፈጸመው ኢሰብአዊ ተግባር በእጅጉ አዝኛለሁ ሲሉ ነው የገለፁት።

ችግሩን በተለያየ መንገድ ለመፍታት የተደረገው ጥረት የሚፈለገውን ውጤት እንዳላመጣም በመግለፅ የጠላቶቻችን ዓላማ በጁንታው ላይ የሠነዘርነውን ብርቱ ኃይል ለመበተን ነው፤ ይህም የሚሳካ አይደለም ብለዋል።

መንግሥት ችግሩን ከመሠረቱ ለመፍታት አስፈላጊውን የተቀናጀ ኃይል እንዲሠማራ አድርጓል፤  የምንፈልገውን ውጤት ለማግኘት ሁላችንም እንደ ከዚህ ቀደሙ በትኩረትና በኅብረት እንድንሠራም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጥሪ አቅርበዋል።