በመዲናዋ 10 ሺሕ ተገጣጣሚ ቤቶችን በአጭር ጊዜ ለነዋሪዎች ለማስተላለፍ እየተሰራ ነው

ሄኖስ ወርቁ

ሚያዝያ 13/2014 (ዋልታ) በአዲስ አበባ የ10 ሺሕ ተገጣጣሚ ቤቶችን ግንባታ በሁለት ዙር በአጭር ጊዜ በማጠናቀቅ ለነዋሪዎች ለማስተላለፍ እየተሰራ መሆኑን የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር አስታወቀ።

የመኖሪያ ቤት እጥረት ችግርን ለማቃለል ተጨማሪ የልማት ፕሮጀክት እየተከናወነ መሆኑን የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ዴዔታ ሄኖስ ወርቁ ገልጸዋል፡፡

ከመኖሪያ ቤት ፈላጊዎች ቁጥር ጋር እጥረቱን ለማቃለል የተገጣጣሚ ቤቶች ግንባታ እየተከናወነ መሆኑን ጠቁመው ከዚህ በፊት በ40/60፣ 20/80 እና 10/90 የቤት ልማት ልማት ፕሮጀክት ሲከናወን ቢቆይም ከቤት ፈላጊው ብዛት አንፃር የፕሮጀክቶች ክንውን በሚፈለገው ልክ አለመሆኑን አስታውቀዋል።

በዚህ ዓመትም በግንባታ ሂደት ላይ የነበሩ 68 ሺሕ ቤቶች ግንባታቸው ተጠናቅቆ ለተጠቃሚ ቢተላለፉም ቀሪ 4 ሺሕ ቤቶች በግንባታ ላይ መሆናቸውን ጠቁመዋል።

በመጀመሪያው ዙር 5 ሺሕ ቤቶችን በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ በማጠናቀቅ ለተጠቃሚው ለማስተላለፍ ግንባታው እየተከናወነ መሆኑን መግለፃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

የመኖሪያ ቤት እጥረት ችግር በመንግሥት ጥረት ብቻ የሚፈታ ባለመሆኑ ሌሎች አማራጮች አንዲኖሩ ድጋፍ እየተደረገ መሆኑንም ጠቅሰዋል።

የውጭ ባለሃብቶች በዘርፉ እንዲሰማሩ ማድረግን ጨምሮ የግል አልሚ ባለሃብቱን ከማኅበራት ጋር በማቆራኘት ለቤት ፈላጊዎች ምላሽ ለመስጠት በትኩረት እየተሰራ መሆኑንም ገልጸዋል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW