በመዲናዋ ለአራት ወራት የሚቆይ የወጣቶች የአረንጓዴ ልማትና የአካባቢ ጥበቃ ስራ ተጀመረ

በአዲስ አበባ ከተማ ለቀጣይ አራት ወራት የሚቆይ የወጣቶች የአረንጓዴ ልማት እና የአካባቢ ጥበቃ ስራ ተጀመረ ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በከተማዋ ለቀጣይ አራት ወራት የሚቆየውን የወጣቶች የአረንጓዴ ልማት እና የአካባቢ ጥበቃ ስራ መርሐግብርን አስጀምረዋል።

በመርሐግብሩ ማስጀመሪያ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ እንደገለፁት አዲስ አበባ ከተማ የቱሪስት መዳረሻ እንድትሆን እና የኢኮኖሚ እንቅስቃሴውን ለማሳደግ ውብ፣ ጽዱ እና ለኑሮ ምቹ መሆን ይኖርበታል ብለዋል።

በቀጣይ አራት ወራት በሚቆየው የወጣቶች የአረንጓዴ ልማት እና የአካባቢ ጥበቃ የበጎፍቃድ አገልግሎት ከ28ሺህ በላይ ሴቶች እና ወጣቶች በሣምንት ሁለት ቀናት እንደሚሳተፉ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ተናግረዋል።

አዲስ አበባ ከተማ የአፍሪካ መዲናነቷን፣ የቱሪዝም እና የዲፕሎማቲክ ማዕከልነቷን ለማስጠበቅ በሚደረገው ጥረት ሁሉም ነዋሪዎች ጽዳቷን በመጠበቅ ድርሻቸውን እንዲወጡ ምክትል ከንቲባዋ ጥሪ አቅርበዋል።

በአዲስ አበባ ከተማ የአካባቢ ጥበቃ እና አረንጓዴ ልማት ኮሚሽን አስተባባሪነት በሁሉም ክፍለ ከተሞች ሴቶች፣ ወጣቶች እና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በችግኝ እንክብካቤ በአረንጓዴ ልማት እና የአካባቢ ጥበቃ ስራ የሚከናወን ይሆናል፡፡

(በአካሉ ጴጥሮስ)