በመዲናዋ የሚዲ-ባስ እና ሚኒ-ባስ ተሽከርካሪዎች የታሪፍ ማሻሻያ ተደረገ

ግንቦት 30/2014 (ዋልታ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ በአዲስ አበባ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ የሚዲ-ባስ እና ሚኒ-ባስ ተሽከርካሪዎች አዲስ የታሪፍ ማሻሻያ አደረገ።

የቢሮው የኦፕሬሽን ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ ዛሬ ለመገናኛ ብዙኃን በሰጡት መግለጫ ተግባራዊ የተደረገው የሚኒ-ባስ ታሪፍ ጭማሪ በኪሎ ሜትር ዝቅተኛው 50 ሳንቲም ሲሆን ከፍተኛው 3 ብር ከ50 ሳንቲም ነው ብለዋል።

በዚህም መሠረት 2 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር 2 ብር ከ50 የነበረው 3 ብር የተደረገ ሲሆን ከፍተኛው ከ27.6 እስከ 30 ኪሎ ሜትር 30 ብር የነበረው ደግሞ 33 ብር ከ50 ሳንቲም ሆኗል።

የሚድ-ባስ የታሪፍ ማሻሻያው ከዚህ ቀደም 4 ብር የነበረው 4 ብር ከ50 ሳንቲም ሲሆን 13 ብር የነበረው ደግሞ 15 ብር ተደርጓል ነው የተባለው።

የታሪፍ ማሻሻያው ከሰኔ 01 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረግ የተገለጸ ሲሆን አፈፃፀሙ በተገቢው እንዲከወን የሕግ አስከባሪ አካላት ሚና የጎላ በመሆኑ የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ ቢሮው አሳስቧል፡፡

ኅብረተሰቡም የወጣውን ትክክለኛ ታሪፍ አውቆ በመክፈልና ከታሪፍ በላይ የሚያስከፍሉ አሽከርካሪዎችን በማጋለጥ በኩል ጥቆማ በመስጠት የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ቢሮው ጥሪ ማቅረቡን የኤኤምኤን ዘገባ አመላክቷል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW