በመዲናዋ ፀጥታና ሰላም ግንባታ ዙሪያ ውይይት እየተካሄደ ነው

ሰኔ 2/2014 (ዋልታ) የአዲስ አበባ ከተማ ሰላም እና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ በፀጥታና ሰላም ግንባታ፣ ፖሊሲና ስትራቴጂ እንዲሁም ረቂቅ ደንብ ላይ ያተኮረ ውይይት ከባለድርሻ አካላትና ምሁራን ጋር እያካሄደ ይገኛል።

መድረኩ በከተማዋ ያለው ሰላም ይበልጥ ተጠናክሮ እንዲቀጥል እና የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመለየት የሰላምና ግንባታ ፖሊሲና ስትራቴጂ ረቂቅ ደንብ ላይ ግብዓት ለማሰባሰብ ያለመ ነው ተብሏል።

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ቀነዓ ያደታ (ዶ/ር) አዲስ አበባ የአፍሪካ ኅብረት መቀመጫ ከመሆኗ ባሻገር የበርካታ ዲፕሎማቶች መቀመጫ እንደመሆኗ መጠን የአዲስ አበባ ሰላም መሆን ለመላው ኢትዮጵያ ሰላም ሚናው የጎላ መሆኑን ተናግረዋል።

የፖሊሲና ስትራቴጂ ደንብ መኖሩ ለከተማዋ ሰላም መረጋገጥ የሚኖረው ድርሻ የጎላ ነው ብለዋል፡፡

የተዘጋጀ የፖሊሲና ስትራቴጂ ረቂቅ ሰነድ ቀርቦ ውይይት እየተደረገበት ሲሆን ሰነዱ ለከተማዋ ካቢኔ ቀርቦ ሕጋዊ ይሆናል ነው የተባለው፡፡

በሱራፌል መንግሥቴ