በሚኔሶታ ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ 30ሺሕ ዶላር ድጋፍ ተደረገ

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ

ኅዳር 14/2014 (ዋልታ) በአሜሪካ ሚኔሶታ ሚድዌስት ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ድጋፍ እንዲሆን ያሰባሰቡትን 30ሺሕ ዶላር ገቢ አደረጉ።

ድጋፉ የተሰበሰበው በሚኔሶታ ሚድዌስት ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ አማካይነት መሆኑን የኮሚቴው ሰብሳቢ ቄስ ፍራንሲስ እስጢፋኖስ መግለጻቸውን ከኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።